August 29 2020
የፊታችን ጳጉሜ 5/2012 ዓ.ም ሥራ ይጀምራል የተባለውን የአዲስ አበባ ኮቪድ-19 ፊልድ ሆስፒታልን ምክትል ጠቅለይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ጋር በመሆን ጎብኝተውታል።
በቦሌ ክፍለ ከተማ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ለኮቪድ 19 ሕክምና አገልግሎት እየተዘጋጀ ያለው የአዲስ አበባ ኮቪድ 19 ፊልድ ሆስፒታል በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስር በጤና ሚኒስቴር አስተባባሪነት በዓለም ምግብ ፕሮግራም እና በዓለም ጤና ድርጅት ድጋፍ የተሠራ ነው።
የሆስፒታሉ ግንባታ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቅቆ የፊታችን ጳጉሜ 5 ሥራ እንደሚጀምር የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሥራ አኪያጅ ዶ/ር ታምሩ አስፋ ተናግረዋል።
ሆስፒታሉ በሙሉ አቅሙ ሥራ ሲጀምር 200 አልጋ እንደሚኖረው ዶ/ር ታምሩ መናገራቸውን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
#EBC
[email-subscribers-form id=”1″]