You are currently viewing ከመጠን በላይ ውፍረት በኮቪድ-19 የሚመጣ ሞትን 48 በመቶ ይጨምራል- አንድ ጥናት

ከመጠን በላይ ውፍረት በኮቪድ-19 የሚመጣ ሞትን 48 በመቶ ይጨምራል- አንድ ጥናት

August 27 2020

ከመጠን በላይ ውፍረት በኮቪድ-19 የሚመጣ ሞትን በ48 በመቶ እንደሚጨምር እና ለበሽታው የሚሰጡ ክትባቶች ብዙም ውጤታማ እንዳይሆኑ እንደሚያደርግ አንድ አዲስ የወጣ ዓለም አቀፍ ጥናት አመለከተ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቁ ባለሞያዎች ያደረጉት ይኸው ጥናት ከመጠን በላይ ክብደት ላላቸው ሰዎች ቫይረሱ ያለው አደጋ ቀደም ሲል ሲታሰብ ከነበረው በላይ ነው ብለዋል።

ጥናቱ በዓለም ባንክ በኩል የተካሄደ ሲሆን መንግሥታት ከመጠን በላይ ውፍረትን መከላከል ላይ እንዲሠሩ የማድረግ ግፊት እንዲበረታባቸው ያደርጋል ብሏል።

አሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የሆነ ከመጠን በላይ ወፍራም  ሰዎች ያለባቸው ቀዳሚ ሀገራት መሆናቸውም ጥናቱ ተመልክቷል።

የአሜሪካ መንግሥት አሐዛዊ መረጃ  ከ40 በመቶ በላይ የሚሆኑ አሜሪካውያን ከመጠን በላይ ውፍረት እንዳለባቸው ያሳያል።

እንግሊዝ ውስጥ ደግሞ ከ27 በመቶ በላይ ጎልማሶች የችግሩ ተጠቂ ናቸው ተብሏል።

አሜሪካ ቻፕል ሂል በሚገኘው የኖርዝ ካሮላይና ዩኒቨርሲቲ የተሠራው ይኸው ጥናት ከመጠን ባላይ ውፍረት ያለባቸው ሰዎች በብዙ መንገድ ከፍተኛ  የኮሮናቫይረስ ተጋላጭነት እንዳላቸው አሳይቷል።

ጥናቱ ከመጠን ባላይ ውፍረት ያላቸው ሰዎች በኮቪድ-19 በሽታ ተይዘው ወደ ጽኑ ሕክምና ክፍል ውስጥ የመግባት እድላቸው 74 በመቶ እንዲሁም በቫይረሱ ለሞት የመዳረግ ዕድላቸው ደግሞ 48 በመቶ መሆኑን አሳይቷል።

ጥናቱን የመሩት በኖርዝ ካሮላይና ዩኒቨርሲቲ ግሊንግስ ዓለም አቀፍ የኅብረተሰብ ጤና ት/ቤት የሥነ ምግብ ትምህርት ክፍል ባልደረባ የሆኑት ፕሮፌሰር ባሪ ፖፕኪን፣ በግኝቱ መደንገጣቸውን ለጋርዲያን ተናግዋል።

ከመጠን በላይ ክብደት ያላቸው ሰዎች በኮቪድ-19 የመሞታቸው እድል ማንም ከሚያስበው በላይ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን መጥቀሳቸውን ዘ ጋርዲያን አስነብቧል።

“ይህ ለእኔ ትልቅ ተፅዕኖ ነው” ያሉት ፖፕኪን “የጥናት ግኝቱ አደጋው 50 በመቶ ጭማሪ እንዳለው ያሳየ ነው። ይህም በጣም አስጨናቂ አሐዛዊ መረጃ ነው። ከጠበቅኩትም በላይ ነው” ብለዋል።

Source :-

https://t.me/jossiale2022

 

[email-subscribers-form id=”1″]

 

[irp posts=”205″ name=”በዱባይ ውሾች የኮሮናቫይረስ ምርመራ እያደረጉ ነው‼️”]

 

Leave a Reply