August 27 2020
የቻይና መንግስት ለ3ኛ ዙር የኮሮናቫይረስ(ሳርስ-ኮቭ2) መከላከያ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ለኢትዮጵያ ለግሷል።
በዚኛው ዙር ድጋፍ 500 ሺህ ሰርጂካል የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል፣ 65 ሺህ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል፣ 10 ሺህ የሜዲካል አልባሳት እና የጫማ መሸፈኛ እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰርጂካል ጓንቶች ተካተውበታል።
የቻይና መንግስት ኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል በምታደርገው ዘርፈ ብዙ ጥረት ድጋፉ እንዳልተለየ እና ወረርሽኙ ወደ አገሪቱ ከገባበት ከመጋቢት ወር ጀምሮ የሚያደርገው ድጋፍ ሳይቋረጥ መቀጠሉንም በአዲስ አበባ የሚገኘው የቻይና ኢምባሲ አስታውቋል።
ሚያዝያ ወር ከቻይና የመጡ የህክምና ቡድን አባላት ለ15 ቀናት በኢትዮጵያ የህክምና ድጋፍ መስጠታቸውም ይታወሳል።
#EBC