የ15 አፍሪካ ሀገራት የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ከ10 ሺህ ተሻግሯል-ሲዲሲ አፍሪካ

August 26 2020

የ15 አፍሪካ ሀገራት የኮሮናቫይረስ (ሳርስ-ኮቭ2) ተጠቂዎች ቁጥር ከ10 ሺህ መሻገሩን የአፍሪካ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ማእከል ሲዲሲ አፍሪካ አስታወቀ፡፡

በመላ አህጉሪቱ አዳዲስ የተጠቂዎች ቁጥር በስፋት እየታየ መሆኑን ሪፖርቱ አመላክቷል።

በዚህም በአፍሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን 195 ሺህ በላይ የደረሰ ሲሆን ከ17 ሺህ በላይ የሟቾች ቁጥር ተመዝግቧል።

እንደ ሪፖርቱ ደቡብ አፍሪካ ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተጠቂዎችን ያሳወቀች ሲሆን፣ ግብፅ፣ ናይጄሪያ እና ሞሮኮ ከ50 ሺህ እስከ 100 ሺህ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና አልጄሪያ ከ20 ሺህ እስከ 50 ሺህ ባለው ውስጥ የሚገኙ ሀገራት ናቸው።

ከዚህ ጋር ተያይዞ እስካሁን ከ921 ሺህ በላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች ማገገማቸው መገለጹን ሲጂቲኤን አስነብቧል።

 

#CGTN

#EBC

 

Subscribe to Receive Free Updates
Loading

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *