You are currently viewing ኮቪድ-19 ጠንካራ የጤና ስርዓት የብሄራዊ ደህንነት ጉዳይ መሆኑን አስተምሮናል- ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ

ኮቪድ-19 ጠንካራ የጤና ስርዓት የብሄራዊ ደህንነት ጉዳይ መሆኑን አስተምሮናል- ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ

August 26 2020

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ኮቪድ-19 ጠንካራ የጤና ስርዓት መኖር የብሄራዊ ደህንነት ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል ።

70ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠና ኮሚቴ ጉባዔ በትናንትናው እለት በቪዲዮ ኮንፍረንስ ተካሂዷል።

በጉባዔው ላይም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በቪዲዮ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን፥ በመልእክታቸውም ባለፉት 8 ወራት ዓለማችን በኮቪድ 19 ምክንያት ተፈትናለች ብለዋል።

በዓለም ላይ በፍጥነት እየተሰራጨ ያለው የኮሮና ቫይረስ በአጭር ጊዜ ውስጥ በዓለም ዙሪያ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎችን አጥቅቷል፤ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሀይወትም ቀጥፏል ሲሉም ተናግረዋል።

የኮሮና ቫይረስ ጤናችንን ብቻ ሳይሆን፣ የአኗኗር ዘይቤያችንን፣ ማህበራዊ እሴቶቻችንን እንዲሁም ኢኮኖሚያችንን በክፉኛ ጎድቷል ያሉ ሲሆን፥ ልጆቻችንን ወደ ትምህርት ቤት አንዳንልክ ከልክሎናል፤ ሰዎች አንድ ቦታ ላይ እንዳይሰበሰቡ እንዲሁም የሚያመልኩበትን መንገድን እንዲቀይሩ አስገድዷል ብለዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስን ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ መሆኑን ካወጀበት ጊዜ አንስቶ የኢትዮጵያ መንግስት የቫይረሱን ስርጭት እና የሚያስከትለውን ጫና ለመቀነስ የተለያዩ እርምጃዎችን ስትወስድ መቆየቱንም አንስተዋል።

 

#FBC

 

[email-subscribers-form id=”1″]

Leave a Reply