You are currently viewing በአፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1.2 ሚሊየን ደርሷል፡፡

በአፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1.2 ሚሊየን ደርሷል፡፡

August 26 2020

በአህጉሪቱ በኮሮናቫይረስ(ሳርስ-ኮቭ2) የሚያዙ ዜጎች ቁጥር በየቀኑ እያሻቀበ ሲሆን እስከዚህ ሰአት ድረስ 1.2 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ ነው የተነገረው፡፡

እንደዚሁም 28 ሺህ ያህል ዜጎች ሂወታቸው ሲያልፍ 922 ሺህ ዜጎች ደግሞ ከበሽታው እንዳገገሙ ነው የአፍሪካ ሲዲሲ መረጃ የሚጠቁመው፡፡

ደቡብ አፍሪካ ከአህጉሪቱ በቫይረሱ በቀዳሚነት የምትገኝ ሀገር ስትሆን 611 ሺህ ዜጎች በቫይረሱ ተይዘውባታል፡፡

በግብጽ ወደ 97 ሺህ የሚጠጉ ዜጎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን በሞሮኮ 53 ሺህ የሚሆኑ ሰዎችም በቫይረሱ መያዛቸውን ነው የተነገረው፡፡

ቫይረሱ በምእራብ አፍሪካ ሀገራትም በፍጥነት እየተዛመተ ሲሆን በናይጄርያ 52 ሺህ ያህል ዜጎች ሲያዙ በጋና ደግሞ ከ43 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዛዋል፡፡

እንደዚሁም በምስራቅ አፍሪካ ሀገራትም የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን ከቀጠናው ሀገራት መካከል በኢትዮጵያ 42 ሺህ የሚጠጉ ዜጎች በቫይረሱ መያዛቸውን አፍሪካ ሲዲሲ ያወጣው መረጃ ይጠቁማል፡፡

 

#EthioFM

Leave a Reply