You are currently viewing ኮቪድ-19 ውሸት ነው ብሎ የሚያምነው ጎልማሳ ባለቤቱ በበሽታው ተቀጠፈች‼️

ኮቪድ-19 ውሸት ነው ብሎ የሚያምነው ጎልማሳ ባለቤቱ በበሽታው ተቀጠፈች‼️

August 25 2020

? ብራየን ሊ ይባላል፡፡ በፍሎሪዳ ውስጥ ታክሲ ነጂ ነው፡፡ ለረዥም ጊዜ ኮሮናቫይረስ የሚባል ነገር የለም፤ ፍጹም ቅጥፈት ነው ሲል ነበር፡፡ ይህን የሚለው ግን ለጨዋታ ድምቀት ብሎ ሳይሆን ከአንጀቱ ነበር፡፡ እንዲያውም ወደ ፌስቡክ እየወጣ ሰዎች በዚህ ኮሮናቫይረስ በሚባል እልም ያለ ውሸት እንዳይታለሉ ይሰብክ ነበር፡፡

? ባለቤቱ ኤሪን ትባላለች ፡፡ ወይም ‹ትባል ነበር› ማለቱ ይሻላል፡፡ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወቷን አጥታለች።
ለብራይን ይህ ትልቁ ቅጣት ሆኖበታል፣ ዛሬ፡፡
ብራይንም ሆነ ባለቤቱ ኤሪን በበይነ መረብ የሚሰራጩ መላምቶች ሰለባ ሆነው ቆይተዋል፡፡

? ‹ኮሮናቫይረስ ብሎ ነገር የለም፡፡ ካለም ጉንፋን ነው፤ ካለም 5ጂ ቴክኖሎጂ የፈጠረው ነገር ነው› ሲሉ ነበር የሚያምኑት፡፡

? ለዚህም ይመስላል ቫይረሱ ከተገኘባቸው በኋላ እንኳን ሐኪም የሚላቸውን ነገር ለመስማት ያልፈቀዱት፡፡

? ሁለቱም ግንቦት ላይ ነበር የታመሙት፡፡ ብራይን በለስ ቀንቶት አገገመ፡፡ ሚስቱ ግን አሸለበች፤ 46 ዓመቷ ነበር፡፡

? ብራይን በሐምሌ ወር ላይ የቢቢሲ እንግዳ ነበር፡፡ ቢቢሲ ያኔ በኮቪድ-19 ዙርያ በሚሰሩ መላምቶችና የሴራ ወሬዎች ዙርያ አንድ ዘገባ እየሰራ ነበር፡፡

? ያን ጊዜ የብራይን ሚስት አልሞተችም ነበር፡፡ ሆኖም በጽኑ ሕሙማን ማገገምያ ክፍል ገብታ ትተነፍስ የነበረው በቬንትሌተር ነበር፡፡

? ኤሪን በፍሎሪዳ ፓስተር ነበረች፡፡ ጤናዋ ግን መልካም የሚባል አልነበረም፡፡ አንደኛ አስም ነበረባት፤ ሁለተኛ የእንቅልፍ እጦት ያሰቃያት ነበር፡፡

? ባሏ ባደረሰባት የአስተሳሰብ ተጽእኖ ምክንያት እና በወቅቱ በቫይረሱ ዙርያ በነበራቸው እምነት ምክንያት ጥንቃቄ እንዳላደረጉ ነው ብራያን ለቢቢሲ የተናገረው፡፡

? ስለዚህ ቫይረሱ እንደያዛቸው ቢያውቁም ሁለቱም ሥራቸውን ቀጥለው ነበር፡፡ እሷም ፓስተርነቷን፣ እሱም ሹፍርናውን፡፡እሷ አልጋ ከያዘች ወዲህም ቢሆን ብራይን መደንገጥ በነበረበት ደረጃ አልደነገጠም፡፡

? መድኃኒት ግዛ ሲባል በመድኃኒቶቹ እምነት ባይኖረውም እያቅማማም ቢሆን ታክሲው እያሽረከረ ይሄዳል፡፡ በጉዞው ላይ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አያደርግ? ማኅበራዊ ርቀቱን አይጠብቅ፡፡ለነገሩ ሁለቱም ግንቦት ላይ የታመሙ ጊዜ ራሱ ቶሎ ሐኪም ለማየት አልሄዱም፡፡

? በብዙ ጥርጣሬና ማመንታት ነበር ምርመራ ያደረጉት፡፡ አለባችሁ ሲባሉም አልደነቃቸውም፡፡ ምክንያቱም ኮሮናቫይረስ ብሎ ነገር የለም ብለው በውስጣቸው ያምኑ ስለነበረ፡፡

? ብራይን አሁን ለቢቢሲ እንደተናገረው ‹ያን ጊዜ ሰው የሚለኝን ሰምቼ ቢሆን ኖሮ…› የሚል ጸጸት አድሮበታል፡፡

‹‹ቫይረሱ እውነት ነው፡፡ ሰዎችን በተለያየ ደረጃ ቢያጠቃም ኮቪድ-19 ሐቅ መሆኑን አምኛለሁ፡፡ አሁን ወደኋላ ሄጄ የምቀይረው ነገር ግን የለም፡፡ አሁንን መኖር ነው የሚኖርብኝ፤ አሁን ላይ ለወደፊት የተሻለ ምርጫ እያደረጉ ከመኖር ሌላ ምን ማድረግ እችላሁ?›› ብሏል ለቢቢሲ፡፡

‹‹ባለቤቴ ላትመለስ ሄዳለች፡፡ አንዳንድ ጊዜ ትናፍቀኛለች፡፡ ወደ ተሻለ ዓለም ተሸጋግራለች ብዬ ማመን ነው የምመርጠው፡፡ ›› ይላል ብራይን፡፡

Source :-

https://www.bbc.com/amharic/news-53900470

[email-subscribers-form id=”1″]

 

 

Leave a Reply