አፍሪካ ከዋይልድ ፖሊዮ ነፃ ስለመሆኗ የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አገኘች‼️

August 25 2020

አፍሪካ “ዋይልድ ፖሊዮ” ከተሰኘው ከአንደኛው የፖሊዮ ቫይረስ አይነት ነፃ ስለመሆኗ የማረጋገጫ የእውቅና የምስክር ወረቀት ዛሬ ተረክባለች።

የፖሊዮ ቫይረስ በአብዛኛው ከ5 ዓመት በታች ያሉ ሕፃናትን የሚያጠቃ ሲሆን አንዳንዴ የነርቭ ሥርዓትን በመጉዳት ሊታከም የማይችል የአካል ጉዳት ያስከትላል።

የመተንፈሻ ጡንቻዎች በቫይረሱ ከተጎዱም ሞትን ያስከትላል።

በአብዛኛው እደሜያቸው ከአምስት አመት በታች የሆኑ ህፃናትን በማጥቃት የሚታወቀው ፖሊዮ ከአመታት በፊት በሺዎች የሚቆጠሩ የአፍሪካ ህፃናትን ሊታከም ለማይችል የአካል ጉዳት ሲዳርግ ቆይቷል።

ይህ ህመም በአሁኑ ወቅት ከአፍሪካ ተጠራርጎ በመጥፋቱ በዓለማችን በአፍጋኒስታን እና በፓኪስታን ብቻ ተወስኖ የሚገኝ በሽታ እንደሆነ ተገልጿል።

ለፖሊዮ እስካሁን መድሀኒት ያልተገኘለት በሽታ ቢሆንም ለህፃናት የተዘጋጁ ክትባቶች እስከ እድሜ ልክ እንደሚያገለግሉ ባለሞያዎች ይገልፃሉ።
ከአፍሪካ ናይጄሪያ ከዋይልድ ፖሊዮ ነፃ አገር በመሆን የመጨረሻዋ እንደሆነች የዘገበው ቢቢሲ ነው።

በአገሪቷ በተካሄደው የክትባት ዘመቻ የፀጥታ ሁኔታቸው አስጊ የሆኑ ቦታዎችንና የገጠር አካባቢዎችን ለማዳረስ ከፍተኛ ጥረትን የጠየቀ ሲሆን፤ በዚህ ሂደትም የተወሰኑ የጤና ባለሙያዎችም በታጣቂዎች ተገድለዋል።

#BBC

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *