August 24 2020
ቻይና ከሐምሌ ወር ጀምሮ ለሐኪሞቿ እና የድንበር ላይ ሠራተኞችየኮቪድ-19 ክትባት እየሰጠች መሆኗን አስታወቀች::
ቻይና ከፍተኛ ተጋላጭነት ላላቸው ባለሞያዎቿ የሙከራ የኮቪድ-19 ክትባት ከሐምሌ ወር ጀምሮ እየሰጠች መሆኗን በአገሪቱ ብሔራዊ የጤና ኮሚሽን ውስጥ የሚሠሩ ከፍተኛ ባለሥልጣን ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ይፋ አድርገዋል።
በቻይና ብሔራዊ የጤና ኮሚሽን የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ልማት ማእከል ዤንግ ዦንግዌይ፣ ክትባቱ ወደ አገልግሎት እንዲገባ ሐምሌ 15 ቀን 2012 ዓ.ም ላይ መወሰኑን ባለፈው ቅዳሜ ዕለት ከሲሲቲቪ ጋር ባደረጉት ቃለ ምለልስ ተናግረዋል።
ዤንግ በዚሁ ወቅት ለቫይረሱ ከፍተኛ ታጋላጭ የሆኑት የሕክምና ሰዎች፣ ወረርሽኝ መከላከል ላይ የተሰማሩ ባለሞያዎች፣ ክሊኒክ ውስጥ ትኩሳት ሕክምና ላይ የተሰማሩ ባለሞያዎች፣ እንዲሁም የጉምሩክ እና ድንበር ሠራተኞች ክትባቱን የመውሰድ ፈቃድ እንዳላቸው ተናግረዋል።
ክትባቱም ሲኖፋርም በተባለው የቻይና ብሔራዊ ባዮቴክ ስብስብ ኩባንያ የተዘጋጀ መሆኑም ተመልክቷል።
የክትባቱ ሦስተኛ ዙር ክሊኒካዊ ፍተሻ በተባበሩት አረብ ኢምሬቶች፣ ፔሩ፣ ሞሮኮ እና አርጀንቲና መከናወኑም ተጠቅሷል።
የክትባቱ ምርምር እና ልማት ቡድን መሪ የሆኑት ዤንግ፣ ክትባቱ “የማኅበረሰብ ንክኪ ለማስቀረት” በቀጣይ ቫይረሱ ሊከሰትባቸው በሚችሉ መጪዎቹ የጸደይ እና ክረምት ወራት መከላከያ ለማድረግ መታሰቡንም ጠቅሰዋል።
ሓላፊው፣ “ለሕክምና ባልደረቦች የመከላከያ ክትባቱን ካደረስን በኋላ የአርሶ አደሮች ግብይት ቦታዎች፣ መጓጓዣዎች እና አንዳንድ የኢንዱስትሪ አገልግሎቶች ላይ ይሰጣል ማለታቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል።
#EBC
#CNN
[email-subscribers-form id=”1″]