ነሃሴ 16/2012 ዓ/ም
የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1፦
በአፋር ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 535 የላብራቶሪ ምርምራ የተደረገ ሲሆን 9 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
አጠቃላይ በአፋር ፦
– 800 በቫይረሱ የተያዙ
– 198 ያገገሙ
በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 742 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 93 ሰዎች በኮሮና መያዛቸው ተረጋግጧል።
አጠቃላይ በሐረሪ ፦
– 789 በቫይረሱ የተያዙ
– 16 ሞት
– 187 ያገገሙ
በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 375 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 10 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 5,441 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 325 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የሁለት (2) ሰዎች ህይወት አልፏል።
በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦
– 62 ከምስራቅ ሸዋ
– 56 ከጉጂ
– 46 ከለገጣፎ ከተማ
– 37 ከአዳማ ከተማ
– 27 ከምስራቅ ሀረርጌ
– 12 ከገላን ከተማ
– 10 ከምዕራብ አርሲ ይገኙበታል።
አጠቃላይ በኦሮሚያ ፦
– 4,468 በቫይረሱ የተያዙ
– 41 ሞት
– 1,384 ያገገሙ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 391 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 16 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
– 14 ከዳምቤ (አጋሎ) ወረዳ
– 1 ከፓዌ ወረዳ
– 1 ከአሶሳ ከተማ
በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 4,442 የላብራቶሪ ምርመራ 121 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።
በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
– 21 ከምዕ/ጎንደር ዞን
– 18 ከሰ/ወሎ ዞን
– 17 ከሰ/ሸዋ ዞን
– 16 ከደሴ ከተማ
– 15 ከዋግ ብ/ሰብ ዞን
– 14 ከደ/ወሎ ዞን
– 8 ከባህር ዳር ከተማ ይገኙበታል።
አጠቃላይ በአማራ ፦
– 1772 በቫይረሱ የተያዙ
– 19 ሞት
– 668 ያገገሙ
ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 307 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 13 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ሁሉም ከማህበረሱ ከተወሰደ ናሙና የተገኙ ናቸው።
አጠቃላይ በድሬዳዋ፦
– 794 በቫይረሱ የተያዘ
– 20 ሞት
– 612 ያገገሙ
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 766 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 113 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በቫይረሱ ተያዙት 113 ሰዎች መካከል አንድ መቶ አምስቱ (105) ከሀዋሳ ከተማ ናቸው።
አጠቃላይ በሲዳማ ፦
– 1,017 በቫይረሱ የተያዙ
– 13 ሞት
– 268 ያገገሙ
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ውስጥ በተደረገው 4,428 የላብራቶሪ ምርመራ 607 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። እንዲሁም በ24 ሰዓታት ውስጥ የ18 ሰዎች ሰዎች ህይወት አልፏል። (12 ከአስከሬን ምርመራ 6 ከጤና ተቋም)
በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2,177 የላብራቶሪ ምርመራ ሃምሳ አንድ (51) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
#Tikvah_Eth