እድሜያቸው 12 እና ከዛ በላይ የሆኑ ልጆች የፊት ጭምብል ማድረግ አለባቸው- WHO

August 23 2020

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመግታት እድሜያቸው 12 እና ከዛ በላይ የሆኑ ልጆች የፊት ጭምብል ማድረግ እንዳለባቸው የአለም ጤና ድርጅት አሳስቧል::

በተጨማሪም እድሜያቸው ከ6-11 የሆኑ ልጆች የፊት ማስክ ማድረጋቸው ለበሽታው እንዳላቸው ተጋላጭነት መወሰን እንደሚገባው “WHO” በፈረንጆቹ ኦገስት 21 በድህረ ገፁ ላይ ከዩኒሴፍ ጋር በመሆን ባወጣው ሰነድ አስፍሯል::

በሰነዱ እንደተገለፀው እድሜያቸው ከ6-11 አመት የሆነ ህፃናት የፊት ጭምብል ማድረግ እንዳለባቸውና እንደሌለባቸው ለመወሰን ልጆቹ የፊት ማስክ መጠቀም መቻላቸው እንዲሁም ማስኩን ማግኘት መቻላቸው እና በቂ የሆነ የአዋቂ እይታ ውስጥ መሆናቸው ላይ ጥገኛ ይሆናል::

 

#WHO

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *