August 23 2020
የአስቸኳይ ጊዜ ክትባት እንዲሰጥ የተፈቀደው በሀገሪቱ የክትባት አስተዳደር ህግ ሲሆን ፣ ሙሉ ፈቀድ ያላገኙ ክትባቶችን ለቫይረሱ ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸው፣ ግለሰቦች ብቻ ይከተባሉ ተብሏል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ቻይና አንድ አዲስ የ ኮሮና ቫይረስ (ሳርስ-ኮቭ2) ክትባት በሰው ላይ እንዲሞከር ፈቃድ መስጠቷ ተነግሯል፡፡ ክትባቱ በነፍሳት ሴል ዉስጥ የተመረተ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ይህም የነፍሳትን ሴሎች በመጠቀም የኮሮ ቫይረስ ክትባት ፕሮቲኖችን ለማሳደግ በቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ ሙከራ ነው፡፡ክትባቱ በእንስሳት ላይ በተደረገ ሙከራ የኮሮናቫይረስ ኢንፌክሽንን ለመከላከል ጥሩ ውጤት ያሳየ ሲሆን ምንም ግልፅ የጎንዮሽ ጉዳት እንዳልተገኘበትም ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
የቻይና ብሔራዊ የህክምና ዉጤቶች አስተዳደር እንደገለጸው ፣ እስካሁን ስምንት የተለያዩ የኮሮና ቫይረስ ክትባቶች የተለያየ ደረጃ ሙከራ ተደርጎላቸዋል፡፡ እነዚህ ክትባቶች ከ 20,000 በላይ ሰዎች ላይ ተሞክረው ደህንነታቸው የተረጋገጠ ሲሆን ዉጤታማነታቸውን ለማረጋገጥ በቅርብ ክትትል እየተሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡
(አልአይን)
#Ethio_Mereja