You are currently viewing 🇮🇹 በጣልያን ኮቪድ-19 ዳግመኛ አንሰራርቷል‼️

🇮🇹 በጣልያን ኮቪድ-19 ዳግመኛ አንሰራርቷል‼️

August 23 2020

👉 ጣልያን ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ 1,071 አዲስ የኮቪድ-19 ታማሚዎችን አግኝታለች:: ይህ ቁጥር ካሳለፍነው የፈረንጆቹ ሜይ ወር በኋላ በቀን ውስጥ የተመዘገበ ከፍተኛው የታማሚዎች ቁጥር ሆኗል ::

👉 ሀገሪቷ ለመጨረሻ ጊዜ ከዚህ ቁጥር የሚበልጥ አዲስ ታማሚ ያስመዘገበችው ባሳለፍነው ማይ 12 ሲሆን በጊዜው ሀገሪቷ በ24 ሰአት ውስጥ ያገኘችው 1,402 ታማሚዎችን ነበር::

👉 ባሳለፍነው የሜይ ወር የጣልያን መንግስት አሳልፎ የነበረውን ለአስር ሳምንታት የቆየ ጥብቅ የእንቅስቃሴ እገዳን በፈረንጆቹ አቆጣጠር በሜይ 18 ማላላቱ የሚታወስ ነው::

👉 ጣልያን በአውሮፓ በኮቪድ-19 በከፍተኛ ሁኔታ ከተመቱ ሀገራት መሀል አንዷ ስትሆን ሀገሪቷ እስካሁን ከ35 ሺህ በላይ ሰዎችን በ ኮሮና ቫይረስ ምክንያት በሞት አጥታለች::

👉 በሀገሪቱ ባሳለፍናቸው ማርች እና አፕሪል ወራት ከፍተኛ የሆነ የሟቾች ቁጥር ካስመዘገበች በኋላ ወረርሽኙን በተወሰነ መልኩ ለመቆጣጠር ችላ ነበር ነገር ግን ባሳለፍነው አንድ ወር ውስጥ በሀገሪቷ በቫይረሱ አዲስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ቀስ በቀስ እየጨመረ ይገኛል::

Leave a Reply