You are currently viewing በኢትዮጵያ የክልል ጤና ቢሮዎች ሪፖርት እና የድሬዳዋ መስተዳደር የኮቪድ-19 መግለጫ!

በኢትዮጵያ የክልል ጤና ቢሮዎች ሪፖርት እና የድሬዳዋ መስተዳደር የኮቪድ-19 መግለጫ!

ነሃሴ 17/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች፦

#Afar

በአፋር ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 445 የላብራቶሪ ምርምራ የተደረገ ሲሆን 6 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

አጠቃላይ በአፋር ፦
– 806 በቫይረሱ የተያዙ
– 212 ያገገሙ

#Harari

በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 718 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 59 ሰዎች በኮሮና መያዛቸው ተረጋግጧል።

አጠቃላይ በሐረሪ ፦
– 848 በቫይረሱ የተያዙ
– 16 ሞት
– 224 ያገገሙ

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 401 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1 ሰው በኮቪድ-19 መያዙ ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 2,727 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 42 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
– 13 ከሰ/ሸዋ ዞን
– 12 ከባህር ዳር
– 8 ከምስ/ጎጃም ይገኙበታል።

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 5,007 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 156 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦
– 27 ከምዕራብ ወለጋ
– 17 ከአደማ ከተማ
– 17 ከምስራቅ ሸዋ
– 11 ከነቀምት
– 10 ጉጂ
– 10 ምስራቅ ሀረርጌ ይገኙበታል።

አጠቃላይ በኦሮሚያ ፦
– 4,624 በቫይረሱ የተያዙ
– 41 ሞት
– 1,444 ያገገሙ

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 380 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 12 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

– 8 ከሆሞሻ ወረዳ
– 3 ከባምቢስ ወረዳ
– 1 ከካማሽ ወረዳ

#Sidama

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 621 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 111 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

– 91 ከሀዋሳ
– 8 ከማልጋ
– 3 ከአለታ ወንዶ ወረዳ
– 3 ከዳራ ወረዳ
– 3 ከአለታ ጩኮ ወረዳ
– 2 አለታ ወንዶ ከተማ

አጠቃላይ በሲዳማ ፦
– 1,128 በቫይረሱ የተያዙ
– 13 ሞት
– 281 ያገገሙ

#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ውስጥ በተደረገው 6,681 የላብራቶሪ ምርመራ 968 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። እንዲሁም በ24 ሰዓታት ውስጥ የ13 ሰዎች ሰዎች ህይወት አልፏል። (10 ከአስከሬን ምርመራ 3 ከጤና ተቋም)

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
– 138 ከንፋስ ስልክ ላፍቶ
– 133 ከአዲስ ከተማ
– 130 ከአራዳ
– 113 ከኮልፌ ቀራንዮ
– 106 ከጉለሌ ይገኙበታል።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1,894 የላብራቶሪ ምርመራ 33 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

– ከጋሞ 14 (6ቱ አርባ ምንጭ ከተማ፣ 5 ካምባ፣ 2 ከጋርዳማርታና 1 ከቦንኬ) ፣
– ከጎፋ 9 ( 9ኙም ከመሎ ወረዳ) ፣
– ከስልጤ 7 (6ቱ ሁልባረግ እና 1 ወራቤ ከተማ) ፣
– ከደቡብ ኦሞ 4 (4ቱም ጂንካ ከተማ) ፣
– ከወላይታ 6 (4ቱ ከሶዶ ከተማ፣ 1 ከሶዶ ዙሪያና 1 ከኪንዶኮይሻ ወረዳዎች )፣
– ከካፋ 3 (3ቱም ከቦንጋ ከተማ) እና  ከደራሼ 1 የተገኘባቸው ዞኖችና ወረዳዎች ናቸው፡፡

#Tikvah_Eth

በኢትዮጵያ-የክልል-ጤና-ቢሮዎች-ሪፖርት-እና-የድሬዳዋ-መስተዳደር-የ-ኮሮና-ቫይረስ-መግለጫ-ነሃሴ-17-2012-1

Leave a Reply