ትንኞቹ እንዲለቀቁ ተወስኗል‼️

August 22 2020

የዘረመል ለውጥ የተደረገላቸው 750 ሚሊዮን ትንኞች በአሜሪካዋ ፍሎሪዳ እንዲለቀቁ ተወስኗል::
እነዚህ ትንኞች በድሬደዋ የተከሰተውን የዴንጌ ትኩሳት አይነት ወረርሺኞችን ለመከላከል የሚያግዙ ናቸው::

ትንኞቹ የሚለቀቁት እንደ ዚካ ቫይረስ እና የዴንጌ ትኩሳት አምጪ ትንኞችን ለመቀነስ ሲሆን ውሳኔው የአካባቢ ደህንነትን ለመጠበቅ ከተቋቋሙ ቡድኖች ከፍተኛ ተቃውሞ እየደረሰበት ይገኛል::

ትንኞቹ የሚለቀቁት እንደ ዚካ ቫይረስ እና የዴንጌ ትኩሳት አምጪ ትንኞችን ለመቀነስ ሲሆን ውሳኔው የአካባቢ ደህንነትን ለመጠበቅ ከተቋቋሙ ቡድኖች ከፍተኛ ተቃውሞ እየደረሰበት ይገኛል::

የአካባቢ ደህንነት አክቲቪስቶች የትንኞቹ መለቀቅ በስነምህዳሩ ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል በማለት ድምፃቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ:: አክቲቪስቶቹ የነዚህ ተባዮች መለቀቅ አዲስ የተዳቀሉ እና ፀረ ተባይን መቋቋም የሚችሉ ተባዮች እንዲፈጠሩ ሊያደርግ ይችላል ቢሉም ተባዮቹን የፈጠረው ድርጅት ግን ተባዮቹ በመንግስት ተቀባይነት ባገኙ ጥናቶች በሰው ላይም ሆነ በስነምህዳሩ ላይ ምንም ጉዳት እንደማያስከትሉ ተረጋግጧል ብሏል::

ተባዮቹ የሚለቀቁት ፍሎሪዳ ኪይስ በሚባሉ ተከታታይ ደሴቶች ላይ ሲሆን የሚለቀቁት በፈረንጆቹ 2021 ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል::

ነገሩ የሆነው እንዲህ ነው ባሳለፍነው የፈረንጆቹ ሜይ ወር የአሜሪካ የአካባቢ ኤጀንሲ (US Environmental Agency) ኦግዚቲክ ለተሰኘ በኢንግሊዝ መቀመጫውን ላደረገ ኩባንያ ዘረመላቸው የተስተካከለ በፆታ ወንድ የሆኑ “ኤዲስ ኢጂፕቲ ሞስኪቶ ” ተባዮችን እንዲያመርት ፈቃድ ሰጠ::

እነዚህ “ኤዲስ ኢጂፕቲ ሞስኪቶ” የተሰኙ ተባዮች ለሰዎች ገዳይ የሆኑ እንደ ቺኩንጉንያ ፣ ዚካ ቫይረስ ፣ ዴንጌ እና የቢጫ ወባ የተባሉ በሽታዎችን የሚያስተላልፉ ናቸው::ነገር ግን እነዚህን በሽታዎች የሚያስተላልፉት ሴቶች ተባዮች ብቻ ናቸው:: ይህም የሚሆነው ሴቶቹ ተባዮች እንቁላል ለመጣል ደም ስለሚያስፈልጋቸው ነው::

እነዚህ የዘረመል ማስተካከያ የተደረገላቸው ወንድ ተባዮች ሄደው ሴቶቹ ተባዮችን እንደሚያጠቁ ይታሰባል:: ታዲያ እነዚህ የተጠቁት ሴት ተባዮች እንቁላል ሲጥሉ የምትፈለፈለው ሴት ከሆነች ዘረመሉ በተስተካከለው የወንዱ ትንኝ ዘር ፈሳሽ ምክንያት የሚፈጠር ፕሮቲን የተፈለፈለችው ሴት መንከሻ እድሜ ላይ ሳትደርስ እንድትሞት ያደርጋል::

 

Source:-

https://www.bbc.com/news/world-us-canada-53856776

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share via
Copy link
Powered by Social Snap