ኮቪድ-19 በአውሮፓ‼️

በአውሮፓ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። በርካታ አገራትም ከወራት በኋላ ከፍተኛ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር መዝግበዋል።

ከዓለም አገራት ቀድማ ክፉኛ በቫይረሱ የተጠቃችው ጣሊያን ከእነዚህ አገራት አንዷ ናት። አገሪቷ ረቡዕ ዕለት ብቻ 642 አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን መዝግባለች። ይህም ከግንቦት ወር መጨረሻ በኋላ የተመዘገበ ከፍተኛው ቁጥር ነው ተብሏል።

በስፔን ረቡዕ ዕለት 3 ሺህ 715 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተገልጿል። አገሪቷ ሰኔ ወር መጨረሻ ላይ ጥላው ከነበረው ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ ከወጣች በኋላ የተመዘገበ ከፍተኛው ዕለታዊ ቁጥር መሆኑ ተነግሯል።

በጀርመንም እንዲሁ ሐሙስ ዕለት ብቻ 1 ሺህ707 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተመዘገቡ ሲሆን ይህም ከሚያዚያ ወር በኋላ በአንድ ቀን የተመዘገበ ከፍተኛው ቁጥር ሆኗል።

#BBC

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share via
Copy link
Powered by Social Snap