ትምህርት ቤቶች ይከፈቱ – የዓለም ጤና ድርጅት እና ዩኒሴፍ

August 21 2020

የዓለም ጤና ድርጅት እና ዩኒሴፍ በአፍሪካ ትምህርት ቤቶች ዳግም እንዲከፈቱ ጥሪ አቅርበዋል::

የዓለም ጤና ድርጅት እና የተመድ የሕፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) በአፍሪካ በኮሮናቫይረስ (ሳርስ-ኮቭ2) ወረርሽኝ ምክንያት ተዘግተው የከረሙት ትምህርት ቤቶች ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ዳግም እንዲከፈቱ መንግሥታት ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ትምህርት ቤቶች ለረጅም ጊዜ ተዘግተው መቆየታቸው ተማሪዎች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያመጣል ያሉት ድርጅቶቹ፣ የኮሮናቫይረስ(ሳርስ-ኮቭ2) በትምህርት ተቋማት ውስጥ እንዳይስፋፋ መንግሥታት በንፅህና መጠበቂያዎች ላይ በቂ ገንዘብ እንዲመድቡ መክረዋል።

ተማሪዎች ለረጅም ጊዜ ቤታቸው ውስጥ በመቆየታቸው ለምግብ እጥረት፣ ያለዕድሜ እርግዝና እና ለቤት ውስጥ ጥቃት እየተጋለጡ መሆኑን ነው ሁለቱ ድርጅቶች ያስታወቁት።

በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር የሆኑት ማሺዲሶ ሞኤቲ፣ “…ትምህርት ቤቶች ለአፍሪካ ሕፃናት እንደ ዋና ከለላም ጭምር የሚቆጠሩ ናቸው… “ብለዋል።

ስለዚህ ሀገራት የቢዝነስ እንቅስቃሴን ደህንነቱ በተጠበቁ መልኩ እንደከፈቱት ሁሉ ትምህርት ቤቶችንም በዚሁ መልኩ መክፈት ይችላሉ ሲሉ ተናግረዋል።

የዩኒሴፍ የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር ሞሐመድ ፎል በበኩላቸው፣ ትምህርት ቤቶች ለረጅም ጊዜ ተዘግተው መቆየታቸው በተማሪዎች መጪ ጊዜ ላይ ከፍተኛ ተግዳሮት ይደቅናል ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

#BBC
https://doctorsonlinee.com/2020/08/20/የኮቪድ-19-ክትባትን-በርካሽ-

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share via
Copy link
Powered by Social Snap