August 21 2020
በሀገራችን በ24 ሰአት ውስጥ ተጨማሪ 1,829 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል ‼️
ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 23,035 የላብራቶሪ ምርመራ 1,829 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም የ17 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 637 አድርሶታል።
በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 377 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው የገገሙ ሰዎችን ቁጥር 13,913 አድርሶታል፡፡
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 37,665 ደርሷል፡፡