You are currently viewing የኮቪድ-19 ክትባትን በርካሽ ‼️ 

የኮቪድ-19 ክትባትን በርካሽ ‼️ 

August 20 2020

ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ክትባትን በርካሽ እንደሚያገኙ ከሚጠበቁ 92 ሃገራት መካከል አንዷ ሆነች::

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2021 እንደሚደርሱ የሚጠበቁ የኮቪድ-19 ክትባቶችን በርካሽ ከሚያገኙ 92 ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሃገራት መካከል አንዷ እንደሆነች ዓለም አቀፉ የክትባቶች ትብብር (ጋቪ) መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

ጋቪ ከቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ደረጃቸውን የጠበቁ አንድ መቶ ሚሊዬን የቫይረሱን ክትባቶች በፍጥነት ለማምረት የሚያስለውን ሰምምነት ሴረም ከተሰኘው የህንድ የክትባቶች አምራች ተቋም ጋር ስምምነት ፈጽሟል፡፡ ሴረም አስትራ ዜናካ እና ኖቫቫክስ በተባሉ የምርምር ተቋማት በመዘጋጀት ላይ ያሉ ክትባቶችን ነው የሚያመርተው፡፡

የጋቪ ቦርድ እውቅና የሰጣቸው 92ቱ ሃገራትም ኮቫክስ በተሰኘው የትብብሩ አዲስ የፋይናንስ ስርዓት በመታገዝ ክትባቶቹን ከሶስት ዶላር (መቶ አስር ብር ገደማ) ባልበለጠ ዋጋ የሚያገኙ ይሆናል፡፡ የስርዓቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተመረጡ 92 ሃገራት ዝርዝርም ባሳለፍነው ሳምንት በጋቢ ቦርድ ጸድቋል፡፡ ከነዚህ ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ነች፡፡

 

Leave a Reply