በኢትዮጵያ በ24 ሰአት ውስጥ ተጨማሪ 1778 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል ‼️

August 20 2020

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 21,456 የላብራቶሪ ምርመራ 1778 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም የ20 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 620 አድርሶታል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 228 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው የገገሙ ሰዎችን ቁጥር 13,536 አድርሶታል፡፡

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 35,836 ደርሷል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share via
Copy link
Powered by Social Snap