August 19 2020
በአፍሪካ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ሞት ሪፖርት ያልተደረገባቸው ሀገራት ኤርትራና ሲሸልስ ብቻ ናቸው፡፡
እስካሁን ድረስ በሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ከኮቪድ-19 ጋር በተገያያዘ ሞት ሲመዘገብባቸው ከኤርትራ እና ከሲሸልስ ግን እስከ አሁን አንድም ሞት አልተመዘገበም፡፡
በኤርትራ እስካሁን 285 ሰዎች በይቫረሱ የተያዙ ሲሆን 248 ከቫይረሱ ሙሉ በሙሉ አገግመዋል፡፡
እንዲሁም 37 ሰዎች ደግሞ በለይቶ ማከምያ ክፍል ህክምናቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡
እንዲሁም በሲሸልስ 127 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ 126 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡
አንድ ሰው ብቻ ነው በለይቶ ማከምያ ክፍል ህክምናውን እየተከታተለ የሚገኝው፡፡
ከአፍሪካ አነስተኛ ሞት የተመዘገበባት ሀገር መካከለኛው ሰሀራ ስትሆን በሀገሪቱ አንድ ሰው ብቻ ነው ለህልፈት የተዳረገው፡፡
እንዲሁም በዚህችው ሀገር አስር ሰዎች ብቻ ናቸው በቫይረሱ የተያዙት፡፡
በጠቅላላው ቫይረሱ በሀገራቸው እንዳለ ሪፖርት ካደረጉ 215 የአለም ሀገራት በቫይረሱ ምክንት ሞት ያልተመዘገበባቸው ሀገራት 22 ብቻ ናቸው ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።
በኢትዮጵያ ደግሞ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስካሁን(12/12/12) ምንም ሞት አልተመዘገበም::
በተጨማሪም እንደክልሉ ጤና ቢሮ ሪፖርት ከሆነ በአሁኑ ሰአት በክልሉ አንድም በቫይረሱ በጽኑ የታመመ ሰው የለም፡፡
#Aljazeera
#EthioFM