The Video Above Shows Chinese Vaccine Trial In Abudabi
August 18 2020
አንድ የቻይና ድርጅት በዓመቱ መጨረሻ የኮቪድ -19 ክትባት ዝግጁ እንደሚሆን አስታወቀ‼️
አንድ የቻይና የመድሃኒት አምራች ድርጅት በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ የኮቪድ -19 ክትባት ዝግጁ ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታወቀ።
የዚህ ሲኖፋርም የተባለው ድርጅት ኃላፊ ሊዩ ጂንግዠን ለኮቪድ -19 ክትባት ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው አንደኛው ክትባት አሁን ላይ በዩናይትድ አረብ ኤምሬቶች ደረጃ ሦስት በሰዎች ላይ በሚደረግ ክሊኒካል ሙከራ ላይ እንደሚገኝ ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል::
ኃላፊው ራሳቸውም ሁለት መጠን [ዶዝ] ክትባት እንደወሰዱና እስካሁን ምንም ዓይነት የጎንዮሽ ጉዳት እንዳልገጠማቸው ለግሎባል ታይምስ ተናግረዋል።
ይህ ክትባት በታህሳስ ወር መጨረሻ ላይ ለሁለት ዶዝ ከ144 ዶላር ባነሰ ዋጋ ለገበያ ይቀርባልም ተብሏል።
#BBC