You are currently viewing አጥንት መሳሳት ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ ስብራቶችን እንዴት እንከላከል?

አጥንት መሳሳት ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ ስብራቶችን እንዴት እንከላከል?

በዶ/ር ሳሙኤል ሀይሉ

August 17 2020
            አጥንት መሳሳት በአብዛኛው አድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ የሆኑ ወገኖችን የሚያጠቃ ሲሆን፥ ለየት ባለ መልኩም ማረጥን (የወር አበባ መቆምን) ተከትሎ በሚከሰቱ የሆርሞን ለውጦች ምክንያት እናቶችን በከፍተኛ ሁኔታ ያጠቃል።
? ከአጥንት መሳሳት ጋር በተያያዘ ለየት ባለ መልኩ የሚጠቁት የሰውነት ክፍሎች የዳሌ አጥንት (hip region bones)፥ የወገብ አከርካሪ አጥንት (lumbosacral spine) የእጅ አንጓ አጥንት (distal radius)፥ እና የአፅመ ወርች አንገት (የትከሻ አጥንት/proximal humerus) ናቸው።
? ከነዚህም መካከል ዛሬ ከአጥንት መሳሳት ጋር ተያይዞ የሚከሰት የዳሌ ማቀፊያ አጥንት ስብራትን (Acetabulum Fracture) እንመለከታለን።
ዳሌ አካባቢ የሚከሰቱት ስብራቶች ከተለመዱት ካንሰሮች ባልተናነሰ ለህይወት አስጊ መሆናቸው በተለያዩ ጥናቶች የተረጋገጠ ሲሆን ፤ የዚህም ዋና ምክንያት የስብራት ሰለባ የሆኑትን ወገኖች መራመድ ባለመቻላቸው እና የአልጋ ቁራኛ ከመሆን ጋር በተያያዘ ከሚከሰቱ የጎንዮሽ ጠንቆችን በማስከተል ነው። እነዚህ የጎንዮሽ ጠንቆች ደም መርጋት፥ የሳንባ አና ኩላሊት እንፌክሽኖች፥ ጡንቻ መሟሸሽ፥ የአጥንት መሳሳት መባባስ፥ የልብ ችግሮች፥ የተለያየ ቦታ የሚከሰቱ ቁስሎችን ወዘተ… ናቸው::
? አጥንት መሳሳትን በመከላከል ሊከሰቱ ከሚችሉ ለህይወት አስጊ ከሆኑ ተያያዥ ስብራቶች አራሳችንን እና ወገን ዘመድን መጠበቅ ይቻላል። ለዚህም የሚሆኑ መከላከያ መንገዶች በ2 ደረጃ ተመድበው ይታወቃሉ።
       ሁለትም የአጥንት መሳሳት መከላከያ ዘዴዎች በሚከተለው መልኩ እናያቸዎለን፤
1) አንደኛው ዘዴ ስብራት ከመከሰቱ በፊት የምናደርገው መከላከል ነው::
(Primary Osteoporosis Prevention)
* ይህ ተመራጭ የሆነው መከላከያ ዘዴ ሲሆን በወጣትነታችን በተለይም (ከ20-30ዓመት) የዕድሜ ዘመናችን ከፍተኛ የሚባለውን የአጥንት ጥንካሬ ደረጃ (Peak Bone Mass) ለማድረስ መጣር አለ የማይባል ዋነኛው አጥንት መሳሳት መከላከያ ዘዴ ነው።
? የካልሲየም እና ቫይታሚን ዲ ምነጭ የሆኑ የተመጣጠኑ ምግቦችን (ማለትም ወተት እና የወተት ተዎፅኦዎች፥ አረንጓዴ ቅጠላ ቅጠል ያላቸው መሰል ምግቦችን በመውሰድ እና አግባብ ያለው የፀሀይ ብርሃን በማግኘት፤
?  የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በተገቢው ሁኔታ በማድረግና ሌሎችንም እርምጃዎችን በመውሰድ
 እንደ አስፈላጊነቱም ቫይታሚን ዲ ከ ካልሲየም(Vitamin D & Calcium supplments) ጋር መውሰድ
? ዕድሜያችን ገፋ እያለ ሲመጣም የአጥንት መሳሳት ደረጃን ምርመራ በሚመከርበት ጊዜ ማድረግ (DEXA scan) (በተለይም ለእናቶች የወር አበባ መቆሚያ እድሜ ላይ በሚደርሱበት እና ከተቻለም ከመቆሙ በፊት):: ቢስፎስፎኔት የሚባሉትን መድሀኒቶች (bisphosphonate) ከቫይታሚን ዲ እና ካልሲየም(Vitamin D & Calcium supplments) ከከሀኪምዎ ጋር በመማከር መጀመር።
2) ሁለተኛው ዘዴ ደግሞ ስብራት ከተከሰተ በኋላ የምናደርገው መከላከል ነው::
(Secondary Osteoporosis Prevention)
? ይኽም ዘዴ ከአጥንት መሳሳት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን እና ከላይ የዘረዘርናቸው ስብራቶች ከፍተኛ አደጋ ሳያጋጥም ሲከሰቱ (Low energy fractures of hip region, lumbosacral vertebrae, distal radius and proximal humerus regions) ስብራቱን በተገቢው ሁኔታ ከመታከም በተጨማሪ ቢስፎስፎኔት የሚባሉትን መድሀኒቶችን (bisphosphonate) ከቫይታሚን ዲ እና ካልሲየም(Vitamin D & Calcium) ጋር በመውሰድ ሌላ የሰውነታችን አጥንት ክፍል ላይ ሊከሰት የሚችልን ስብራት መከላከያ መንገድ ነው።
እነዚህ ስብራቶች ሲከሰቱም በጊዜው ትክክለኛ ህክምናን በማድረግ (በተለያየ ጊዜ ስለ እያንዳነዱ ስብራት ህክምና ተመልሰን እናያለን) የስብራቱ ባህሪ በሚፈቅደው እና ስብራቱ በቀዶ ህክምና ከተሰራም እንደ ቀዶህክምናው ባህሪ በተቻለ ፍጥነት በመንቀሳቀስ እና ሁለኛውን አጥንት መሳሳት መከላከያ ዘዴ በመከተል የእናት አባቶቻችንን እና ወገን ዘመዶቻችንን ህይወት መታደግ ያስችለናል።
ለዚህም ምሳሌ ይሆን ዘንድ ለዛሬው በ 73 ዓመት አባት ላይ ከአጥንት መሳሳት ጋር በተያያዘ የተከሰተን የዳሌ ማቀፊያ አጥንት ስብራት በትንሸ ጠባሳ ህክምናን (Acetabulum Fragility Fracture treated with Minimal Invasive Percutneous Fixation) ያገኙ ሲሆን፥ ያላቸውን ውጤት እና የሳቸውን መልዕክት እንመለከታለን።
በትንሽ ጠባሳ የሚደረግ ቀዶ ህክምና (Minimal Invasive Surgery) ዘዴ በተሎ ተነስተው እንዲራመዱ እና የማገገም ሂደታቸውንም የተሳለጠ እንዲሆን ይረዳል። ከላይም እንደጠቀስነው ከአልጋ መዎል ጋር ተያይዘው የሚመጡ ጠንቆችንም ይቀንሳል።
Source:-Hakim
Copyright :-

Leave a Reply