August 16 2020
ሙዝን መመገብ በርካታ የጤና ጥቅሞች አሉት::
✍️ ከሌሎች የፍራፍሬ አይነቶች አንፃር በዋጋ ረከስ ያለውና በበርካታ ሰዎች ዘንድ አነስ ያለ ቦታ የሚሰጠው ሙዝ በርካታ የጤና በረከቶችን ይዟል::ሙዝ በንጥረ ነገር ይዘታቸው ከበለፀጉ ፍራፍሬዎች አንዱ ሲሆን በውስጡም በርከት ያሉ እንደ ማግኒዚየም፣ ፓታሲየም፣ አይረን፣ ዚንክ፣ አይወዲን እና ቫይታሚን ኤ፣ቢ፣ኢን ይዟል።
✍️ ወደ ጤና ጥቅሞቹ ከመግባታችን በፊት በዋጋ ረከስ ያለውን ሙዝ በዋጋ ውድ ከሆነው ፖም ጋር በሚይዟቸው ንጥረነገሮች እናወዳድራቸው::
አንድ ሙዝ በውስጡ የፖምን 4 እጥፍ ፕሮቲን፣ 2 እጥፍ ካርቦሃይድረት፣ 3 እጥፍ ፎስፈረስ፣ 5 እጥፍ vit A እና ብረት(IRON)፤ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ ፖታሽየም የያዘ ነው:: ሙዝ በውስጡ የያዛቸው ተፈጥሮአዊ የስኳር ወይም የጣፋጭ ምንጭ የሆኑት ግሉኮስ፣ ስክሮስ፣ እና ፍሩክቶስ የተባሉት ንጥረነገራት ከሙዝ የፋይበር (የቃጫነት) ተፈጥሮ ጋር ተዳምረው መጠነሰፊ ጠቀሜታዎችን ይሰጣሉ። ስለዚህ ሙዝ በውስጡ የካርቦሃይድሬት ንጥረነገሮችን የያዘ በመሆኑ ከፍተኛ ሃይል እንድናገኝ ይረዳናል። አንድ ጤነኛ ሰው ሁለት ሙዝ በልቶ በሚያገኘው ሃይል ለዘጠና ደቂቃ አድካሚ የጉልበት ሥራዎችን መሥራት ይችላል::
ሙዝ ታዲያ ሀይል ከመስጠት በተረፈ እጅግ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎችም አሉት፡፡ ሙዝ ከምግብ ይዘቱ በተጨማሪ ለተለያዩ በሽታዎች ፈውስ ሊያስገኙ የሚችሉ ንጥረ ነገሮችንም አካቶ ይዟል። እነዚህ ንጥረነገሮች ለበርካታ በሽታዎች ፈውስ ከመሆናቸውም በላይ፣ በሽታው ከመከሰቱም በፊት ለመከላከል የሚያስችለንን አቅም ያጐናጽፉናል፡፡
ከበርካታ የሙዝ ጠቀሜታዎች መካከል ጥቂቶቹን ከዚህ እንደሚከተለው ለማየት እንሞክራለን፡፡
1. የደም ግፊት መጠን ለመቀነስ ይረዳል
አንድ መካከለኛ መጠን ያለው ሙዝ የሚይዘው የሶዲየም መጠን 1 ሚ.ግ ገደማ ብቻ ነው:: ሙዝ በተፈጥሮው በውስጡ ዝቅተኛ የጨው መጠን እና ከፍ ያለ የፖታሺየም መጠን መያዙ የደም ግፊትን ለማረጋጋት ይረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በውስጡ ያለው ፖታሺየም የደም ግፊትን ለማስተካከልና በግፊት ሳቢያ የሚከሰቱ ከባድ የጤና ችግሮችን ለመከላከል ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡
2. ስትሮክን ለመከላከል
በሙዝ ውስጥ ያለው ፖታሺየም፣ የደም ሥርዓትን በማስተካከል ባልታሰበ ሁኔታና በድንገት የሚከሰተውን የስትሮክ ችግር ለመከላከል ያግዛል። ሙዝ በሰው ልጆች የአመጋገብ ሥርዓት ውስጥ ተካቶ ዘወትር ለምግብነት የሚውል ከሆነ፣ በስትሮክ ምክንያት የሚመጣውን ድንገተኛ ሞትና የአካል ጉዳት ከ50-60 በመቶ ለመቀነስ ያስችላል፡፡
3. ለአእምሮ ጤንነት
አንድ መካከለኛ መጠን ያለው ሙዝ በውስጡ በአማካይ 467 ሚሊ ግራም ፖታሺየም ንጥረነገርን ይይዛል::
ይህም ንጥረ ነገር የአንጐልን የሥራ ብቃት ለማሻሻል እና ለማሳደግ እንዲሁም ጤናማ አዕምሮ እንዲኖረን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ በተጨማሪም ሙዝ አእምሮ እንዲነቃቃ ያግዛል::
4. ለሆድ ያለው ጠቀሜታ (ለጨጓራ ህመም እና ለሆድ ድርቀት)
ብዙዎች ሙዝ ከበድ ያለ ምግብ እንደሆነ በማሰብ፣ ሙዝ የጨጓራ ህመማችንን እንደሚያባብስብን ስንናገር እንደመጣለን፡፡ ይሁን እንጂ ሳይንስ እንደሚለው ሙዝ ለጨጓራ ችግሮች ሁነኛ መፍትሔ ነው። ሙዝ በባህርይው በጣም ለስላሳ በመሆኑ በጨጓራ ላይ መጨናነቅን የማይፈጥር ሲሆን የጨጓራ አካባቢን በመሸፈን፣ የጨጓራ ውስጥ አሲድን በማስተካከልና በማመጣጠን የጨጓራ ቁስለት እንዳይፈጠር ለማድረግ ያስችላል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በሙዝ ውስጥ የሚገኘው ፋይበር ለምግብ መፍጨት ሥርዓታችን ከፍተኛ ጠቀሜታን ይሰጣል፡፡ የምግብ መፍጨት ሥርዓትን የሚያከናውኑት የሰውነታችን ክፍሎች በቂ የውሃ መጠን እንዲኖራቸው በማድረግ ሆድ ድርቀትን ይከላከላል፡፡ አንጀት የተለሳለሰ እንዲሆን በማድረግ ከሰውነታችን መውጣት የሚገባቸው አላስፈላጊ ነገሮች (ቆሻሻዎች) እንዲወገዱ ለማድረግ ይረዳል፡፡
ሙዝ ከዚህም ባለፈ የአንጀት ቁስለትን እንደሚከላከል ጥናቶቾ ያሳያሉ::
5. ለድብርት
ሙዝ በውስጡ የሚይዘውና ትራይፕቶፋን የተባለው ንጥረ ነገር በሰውነታችን ውስጥ ሴሮቶኒን የባለ ሆርሞን እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡
ይህ ሆርሞን አይነተኛ ተግባሩ ሰውነታችንን ከድካምና ከድብርት በማላቀቅ ወደተሻለ ስሜት ውስጥ እንድንገባ ማድረግ ነው፡፡
7. ለስኳር ህመም
ሙዝ በውስጡ ከፍተኛ ቫይታሚን B6 የያዘ ነው። ይህም በደም ውስጥ የሚኖረውን ከፍተኛ የስኳር መጠን እንዲቀንስ በማድረግ፣ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር ያስችለናል፡፡ ከስኳር መብዛት ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን የጠዋት ህመምንም ያስቀራል፡፡
8. ሙዝና ደም ማነስ
በሙዝ ውስጥ የሚገኘው የብረት ማዕድን ጠቀሜታው በደማችን ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው የሔሞግሎቢን ምርት እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡ ይህም በሔሞግሎቢን እጥረት ሳቢያ የሚከሰተውን የደም ማነስ እንዳይከሰት ያደርጋል፡፡
9. ሙዝ ለስካር
ሙዝ ከወተትና ከማር ጋር ተደባልቆ ለምግብነት ሲውል በከፍተኛ መጠጥ ወይም በስካር ሳቢያ የሚከሰትን ሃንግኦቨር (ያደረ ድምር) በቀላሉ ያስወግዳል፡፡ በመጠጥ ሳቢያ የተጐዳን ሰውነት እንዲነቃቃና ብርታት እንዲያገኝ በማድረግ ረገድም ሙዝ ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል፡፡ የሲጋራ እና መሰል ሱሶች ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ሱሱን ለማቆም እንዲችሉ ሙዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡
10. ለሞቃታማ አየር
በሞቃታማ የአየር ንብረት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ሙዝን ቢመገቡ ሰውነታቸው ሙቀቱን እንዲቋቋም በማድረግ፣ የተረጋጋና የተስተካከለ የሰውነት ሙቀት እንዲኖረን ያደርገናል፡፡
የሙዝ ተጨማሪ ጠቀሜታዎች
👉 በሽታ የመከላከል አቅምዎን ይጨምራል።
👉በወባ ትንኝ የተነደፈ ሰው ወይንም በማንኛውም ተናካሽ ወይም ተናዳፊ ነፍሳት የተነደፈ (የተነከሰ) ሰው በሙዝ ልጣጭ የውስጠኛው ክፍል የተነደፈበትን (የተነከሰበትን) ቦታ በደንብ በማሸት እብጠቱን መቀነስ ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ንድፍያው (ንክሻው) የፈጠረበትን የማቃጠልና የመለብለብ ስሜት ለማስወገድ ይችላል፡፡
👉 ሰውነትዎ በድካም ወይም በህመም ከተጐዳና የምግብ ፍላጐት ከሌለዎ አንድ ሙዝ እንደምንም ይመገቡ፡፡ ሰውነትዎ ሲበረታና የምግብ ፍላጐትዎ ሲጨምር ይታወቅዎታል፡፡
👉 ጥርስን ያነጣል!!
ጥርስዎን ሁልጊዜ ሲቦርሹ ለሁለት ደቂቃ ያህል በሙዝ ልጣጭ/ልጫ (ከልጣጩ በውስጥ በኩል ባለው ነጭ ክፍል) ጥርስዎን ይሹት ከዚያም አስደናቂ ለውጥ ያገኙበታል።
👉 በተለያዩ ነፍሳቶች ሲነከሱ ቁስልዎን ያስታግስልዎታል!! ነፍሳቱ የነከስዎት ቦታ ላይ በሙዝ ልጫ(ከልጣጩ በውስጥ በኩል ባለው ነጭ ክፍል) በማሸት የሚኖረውን እብጠትና ህመም መቀነስ ይቻላል።
👉 የተጎዳን የሰውነት ቆዳን ያስተካክላል!!
ሙዝ የተበላሸ ወይም የተጐዳ የፊት ቆዳን በሚያምር አዲስ የፊት ቆዳ የመተካት ምትሀታዊ ሀይል አለው።
👉የፊት መሸብሸብ ወይም መጨማደድን ይከላከላል!!
ሙዝ ከፍተኛ የክሬምና የተፈጥሮ ማር ካላቸው ምግቦች የሚመደብ ሲሆን አንዳንድ ሴቶች የፊት መሸብሸብን ለመከላከል ሲሉ ከሙዝ የተሰሩ የፊት ክሬሞችን በሳምንት ለ3 ጊዜ ያህል ይጠቀማሉ።
👉 የቆዳ መሰንጠቅን ይከላከላል!!
የሰውነት ቆዳዎ እያሳከክዎትና እየተሰነጣጠቀ ተቸግረዋል? ህመምዎ(ችግርዎ) ይገባኛል፤በጣም እድለኛ ነዎት!! እንደዚህ ያድርጉ የተሰነጠቀውን የሰውነትን ቆዳ በሙዝ ልጫ(ልጣጭ) ይሹት እንደዚያ ሲያደርጉ በሙዙ ልጫ ላይ ያለው ተፈጥሮአዊ ኢንዛይም በተሰነጠቀው ቆዳዎ ላይ በመግባት ስራውን ይሰራል ማለት ነው።
👉 ክንታሮትን ያድናል!!
ሙዝ በፓታሲየም የበለጸገ ነው።ይህ ንጥረ ነገር ክንታሮትን የማዳን አቅም አለው ስለዚህ ሙዝ ተፈጥሮአዊ የክንታሮት መድሀኒት ሆኖ ያገለግላል።
👉ሰውነታችን በስለት ሲቆረጥ ወይም ሲያብጥ የማዳን ሀይል አለው!!
ሙዝ ሰውነታችን በግጭት ወይም በሌላ ምክንያት ሲያብጥ ወይም ስለት ነገር ሲቆርጠን በውስጡ ፓታሲየም የተባለ ንጥረ ነገር ስላለው ሰውነታችን ለማገገም የሚያደርገውን ሂደት ያግዛል ወይም ያፋጥነዋል።
👉 የወር አበባን ተከትሎ የሚመጣ የስሜት መለዋወጥን ይቀንሳል