You are currently viewing የኮሮናቫይረስ ክትባት በፍትሃዊ መንገድ ለአፍሪካ ሀገራት ሊሰራጭ ይገባል- የዓለም ጤና ድርጅት

የኮሮናቫይረስ ክትባት በፍትሃዊ መንገድ ለአፍሪካ ሀገራት ሊሰራጭ ይገባል- የዓለም ጤና ድርጅት

የኮሮናቫይረስ ክትባት በፍትሃዊ መንገድ ለአፍሪካ ሀገራት ሊሰራጭ እንደሚገባ የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

በአፍሪካ ያለው የኮሮና ቫይረስ አሁናዊ ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ተከትሎ የአህጉሪቱ ሀገራት ክትባቱን እኩል ሊያገኙ ካልቻሉ አስቸጋሪ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ማሺዲሶ ሞዬቲ ገልጸዋል።

ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የአፍሪካ ሀገራት በቫይረሱ ዙሪያ ምርምር በማድረግ እና ክትባቱን ለሀገራቸው ለማዋል ሰፊ ስራ እያከናወኑ ካሉት የተሻለ ገቢ ያላቸው የአፍሪካ ሀገራት እኩል ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚገባ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

የየሀገራቱ መንግሥታት ህዝባቸውን ከወረርሽኙ ለመከላከል በሚያደርጉት ጥረት ጎን ለጎን ሌሎች ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ሀገራትንም ታሳቢ ያደርጋሉ ሲሉ ተስፋ እንደሚያደርጉ ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ገልጸዋል።

በዋናነት በዓለም ላይ ያሉ የትኛውም ደሀ ሀገራት የሚገኘውን ክትባት ማግኘት ካልቻሉ የበለጸጉ ሀገራት ከቫይረሱ ጥቃት ማምለጥ እንደማይችሉ ማሰብ የግድ እንደሚላቸው አክለዋል።

በአፍሪካ ያለው የኮሮና ቫይረስ የተጠቂዎች ቁጥር ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ የደረሰ ሲሆን ከ23 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል፡፡

 

©EBC

Leave a Reply