You are currently viewing ሰባት የአፍሪካ አገራት የኮቪድ-19 አንቲቦዲ ምርመራ ሊጀምሩ ነው‼️

ሰባት የአፍሪካ አገራት የኮቪድ-19 አንቲቦዲ ምርመራ ሊጀምሩ ነው‼️

August 14 2020

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአፍሪካ አህጉር ያለበትን ደረጃ ለማወቅ ሰባት የአፍሪካ አገራት ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ የኮቪድ-19 አንቲቦዲ ምርመራ ሊያካሂዱ መሆኑን የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል ሐሙስ ዕለት አስታውቋል።

-የአንቲቦዲ ምርመራው ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘው በተፈጥሮ መከላከያ መንገድ ተዋግተው ማሸነፍ አለማሸነፋቸው የሚለይበት ዘዴ መሆኑ ተመልክቷል።

-“በአህጉሪቱ ውስጥ ምርመራውን ለመጀመሪያ ጊዜ ሊያደርጉ የተዘጋጁ ሀገራት ላይቤሪያ፣ ሴራሊዮን፣ ዛምቢያ፣ ዚምባቡዌ፣ ካሜሩን፣ ናይጀሪያ እና ሞሮኮ” ናቸው ሲሉ መቀመጫውን አዲስ አበባ ያደረገው የማእከሉ ሓላፊ ጆን ንኬንጋሶንግ ገልጸዋል።

-ምዕራባውያን መንግሥታት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎቻቸውን መልሰው ለመክፈት እንዲረዳቸው የአንቲ ቦዲ ምርመራዎችን በማድረግ ምን ያህል ዜጎቻቸው በበሽታው እንደተያዙ ለማወቅ እንደሚጠቀሙበት ሮይተርስ ዘግቧል።

-በአፍሪካ እስካሁን ድረስ ለ9 ነጥብ 4 ሚሊየን ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ የተደረገ ሲሆን፣ ይህም ባለፈው ሳምንት ከነበረው 10 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ንኬንጋሶንግ ተናግረዋል። በመከናወን ላይ ያሉት ምርመራዎች በአሁኑ ሰዓት ምን ያህል ሰዎች ኮቪድ-19 በሽታ አለባቸው የሚለውን ለማወቅ ያስችላሉ ተብሏል።

-በአህጉሪቱ የተወሰደው መጠነኛ የለይቶ ማቆያ እርምጃ ወረርሽኙ የከፋእንዳይሆን ቢያደርግም፣ በበርካታ ሀገራት ውስጥ ያለው የምርመራ መጠን ዝቅተኛነት በሽታው ሪፖርት ከሚደረገው የበለጠ ሊሆን እንደሚችል ባለሞያዎች ገልጸዋል።

-በሮይተርስ አሐዛዊ መረጃ መሠረት እስከ ዛሬ ድረስ በአፍሪካ ከአንድ ሚሊየን በላይ የኮቪድ-19 ሕሙማን ተመዝግበዋል፤ 24 ሺህ 113 ሞቶች ተከስተዋል። በአሁኑ ወቅት 25 ሀገራት ድንበሮቻቸውን ሙሉ በሙሉ እንደዘጉ ሲሆን፣ 23 ሀገራት ደግሞ በመግቢያ በሮቻቸው ላይ ምርመራዎችን በማካሄድ ላይ መሆናቸውን ንኬንጋሶንግ ጠቁመዋል።

-በድንበሮች አካባቢ የሚከናወኑ ምርመራዎችን በማፋጠንእንቅስቃሴዎች እንዲቀላጠፉ ከእውቅና ምስክር ወረቀት መስጠት ጋር ማጣጣም ይገባል ብለዋል።

©EBC

Leave a Reply