You are currently viewing መንግስት ለጤና  ባለሙያዎች ደህንነት ትኩረት እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር አሳሰበ!

መንግስት ለጤና ባለሙያዎች ደህንነት ትኩረት እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር አሳሰበ!

August 14 2020

የሰውን ህይወት ለመታደግ እየሰሩ የሚገኙ የህክምና ባለሙያዎችን፣ መንግስት ትኩረት እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር እና የኢትዮጵያ የጤና ክብካቤ ፌዴሬሽን ጠይቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ፕሬዚዳንት ፣ዶ/ር ተግባር ይግዛው በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በዕየለቱ ሲነገር ፣ በህክምና ሙያ ላይ ያሉ ባለሙያዎች በቫይረሱ ሲጠቁ መረጃው ይፋ እንደማይደረግ ተናግረዋል።

ግዳጅ ላይ ያሉ የጤና ባለሙያዎችን በተመለከተ በለይቶ ማቆያ ምን ያህል እንዳሉ ፣ ምን ያህሉ ደግሞ በጽኑ የታመመ ዶክተሮች ፣ ነርሶች ፣ የፋርማሲ ባለሙያ እና በጤና ተቋም የሚሰሩ ሌሎች ባለሙያዎች ያለበት የጤና ሁኔታ የሚገልጽ ወቅታዊ መረጃ የለም፡፡

ታዲያ መንግስት የሰው ህይወት ለመታደግ የህክምና ባለሙያዎች ላይ ትኩረት መስጠት እንደሚገባውም ዶክተር ተግባር ጠይቀዋል፡፡

ወቅታዊ መረጃ ባይሆንም ከዚህ በፊት በሀገራችን በየዕለቱ ከሚወጡት የኮሮናቫይረስ ተያዥ ቁጥር ውስጥ 5 በመቶ የሚሆኑት የጤና ባለሙያዎች ነበሩ ብለዋል ዶ/ር ተግባር ፡፡

የኢትዮጵያ የጤና ክብካቤ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ዶክተር ማርቆስ ፈለቀ በበኩላቸው የጤና ባለሙያዎችና በጤና ተቋመት የሚሰሩ ሌሎች ባለሙያዎች፣ ምንም ያህል ጥንቃቄ ቢያደርጉ ተጋልጭ ናቸው፤ በመሆኑም ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ዶክተር ማርቆስ አሁን ያለው መዘናጋት በተመከተ አላስፈላጊ ዋጋ እንዳያስከፍለን የቅድመ መከለከል ስራው መረሳት የለበትም ሲሉም አሳስበዋል፡፡

በኮሮናቫይረስ የተያዙ እና በጽኑ የታመሙ ሀኪሞች እንዲሁም በጤና ተቋማት የሚሰሩ ሌሎች ባለሙያዎች፣ ምን ያህል እንደሆኑ ወቅታዊ እና አሁናዊ መረጃ ከጤና ሚኒስቴር ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም፡፡

Leave a Reply