በዱባይ ውሾች የኮሮናቫይረስ ምርመራ እያደረጉ ነው‼️

እነዚህ የሰለጠኑ ውሾች በዱባይ በሚገኙ አየር ማረፊያዎች የተበተኑ ሲሆን ውሾቹ ከመንገደኞች የተወሰዱ ናሙናዎችን በማሽተት መንገደኞቹ ኮሮናቫይረስ እንዳለባቸው እና እንደሌለባቸው ይመረምራሉ::

ሌላው አስገራሚ ነገር ደግሞ ውሾቹ የአንድ መንገደኛ ናሙናን ለመመርመር ከአንድ ደቂቃ በታች መፍጀታቸው ነው::
ውሾቹ ከመንገደኞቹ ጋር ምንም አይነት ንክኪ የሌላቸው ሲሆን ምርመራውን የሚያደርጉት በተለየ ክፍል ውስጥ ነው:: ሆኖም ግን ውሾቹ ዩ.ኤ.ኢ ከኮሮናቫይረስ ጋር ለምታደርገው ትግል ተጨማሪ መሳሪያ ሆኑ እንጂ ብቸኛ መሳሪያ አይደሉም:: ከአፕሪል አንድ ጀምሮ ወደዩኤኢ የሚገቡ መንገደኞች ሁሉ ከኮቪድ-19 ነፃ መሆናቸውን የሚያሳይ ወረቀት መያዝ አለባቸው:: እንዲሁም ከተመረጡ ሀገራት የሚመጡ መንገደኞች ወደ ሀገሪቱ ሲገቡ የPCR ምርመራ ይደረግላቸዋል::

 

ከዚህ ቀደም በዩኒቨርስቲ ኦፍ ቬተርነሪ ሜዲስን ሀኖቨር በተመራ አንድ ፕሮጀክት በጀርመን መከላከያ የሰለጠኑ ውሻዎች በ1 ሳምንት ልምምድ ብቻ ኮሮናቫይረስን በማሽተት ለመለየት ችለው እንደነበር ይታወሳል::

አሁን ደግም በኢንግሊዝ ሀገር የሚገኘው ዱርሃም ዩኒቨርስቲ ውሾች ኮሮናቫይረስን ማሽተት መቻላቸውን ለመፈተሽ ለበጎ ፈቃደኞች ጥሪ አቅርቧል። ተመራማሪዎች በእንግሊዝ መለስተኛ የኮቪድ-19 ምልክት ያለባቸውን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ምርመራ ለማድረግ ወይንም ባለፉት 24 ሰዓታት ምርመራ ያደረጉትን ለመመልመል ይፈልጋሉ። በጎ ፈቃደኞቹ በትንፋሻቸው እንዲሁም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ለሶስት ሰዓት በማድረግ፣ ከናይለን የተሰራ ካልሲ እንዲሁም ቲ ሸርት ለ12 ሰዓት በማድረግ የአካላቸውን ጠረን ናሙና የሚሰጡ ይሆናል።

Leave a Reply