August 12 2020
በአሜሪካ ከ900 በላይ በቫይረሱ ለተያዙ ሰዎች የህክምና እርዳታ የሚሰጡ የጤና ባለሞያዎች በኮቪድ-19 ተይዘው ህይወታቸው እንዳለፈ በትናንትናው እለት ዘጋርዲያን እና ኬኤችኤን ይፋ ያደረጉት የመረጃ ማቆሪያ (Database) አመልክቷል::
በአሜሪካ ደቡብ እና ምዕራብ ክፍል የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች ባጋጠማቸው እራስን ከቫይረሱ የመጠበቂያ እቃዎች ማለትም የጓንት ኤን-95 ማስክ እና ገዋን እጥረት ምክንያት አሁንም ህይወታቸው አደጋ ላይ ወድቋል::
ከህዝብ ውስጥ ከማህበራዊ ሚዲያዎች ፣ ከቀብር ስርአት አስፈፃሚ ድርጅቶች ፣ ከሰራተኞች ማህበራት እንዲሁም
ከትናንሽ ሚዲያዎች በተሰባሰበው መረጃ መሰረት 922 የጤና ተቋማት ሰራተኞች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል::
ከ50 በላይ በሆኑ ጋዜጠኞች የተቋቋመ ቡድን ለወራት የሞቾቹ የሞት ምክንያት እውነት ቫይረሱ መሆኑን ያጣራ ሲሆን 922ቱም የጤና ተቋማት ሰራተኞች በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ጋር በቀጥታ ንክኪ ነበራቸው አልያም በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች የሚታከሙበት ቦታ ይሰሩ እንደነበር ማረጋገጥ ችለዋል::
https://www.theguardian.com/us-news/2020/aug/11/covid-19-healthcare-workers-nearly-900-have-died