Updated on April 25 2021
የባህል መድሀኒቶች ንጉስ (ጋርድኔላ ሉሲደም መሽሩም)
ይህ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ስሙ የገነነው የፈንገስ አይነት ስሙ ጋኖደርማ ሉሲደም ይባላል:: ይህ መሽሩም ፋን የመሰለ ቅርፅ ያለው እና በመጠን ተለቅ ያለ ሲሆን በጣት ደግሞ ሲነካ ደግሞ ለስለስ የሚል መሽሩም ነው:: ይህ ጋኖደርማ የተሰኘ መሽሩም ጥንታዊ ቻይናን ጨምሮ በተለያዩ የእስያ ሀገራት ለብዙ ምዕተ አመታት ጤናን እና እረጅም እድሜን ለማግኘት ብለው ሰዎች ሲጠቀሙበት የኖረ ፈንገስ ነው:: ሉሲደም የሚለው ደግሞ ሉሲደስ ከተባለው የላቲን ቃል የመጣ ሲሆን የሚያብረቀርቅ ማለት ሲሆን ይህም ስያሜ የተሰጠው ፈንገሱ ቫርኒሽ የተቀባ የሚመስል አንፀባራቂነቱን ለመግለፅ ነው::
ይህ ገበያው የጦፈለት የፈንገስ አይነት በአንዳንድ የእስያ ሀገራት ውስጥ በተለያዩ ስሞች ይጠራል:: በቻይናውያን ዘንድ ይሄ ” ጋርድኔላ ሉሲደም ፈንገስ “ሊንግዝሂ ተብሎ ሲጠራ ይህም ስም መንፈሳዊ ሀይልንና ዘለአለማዊነትን የሚወክል ነው:: ጃፓኖች ደግሞ የፈንገሱን ቤተሰብ ሪሺ ወይም ማኒንቴክ ብለው ይጠሩታል:: በሌሎች አንዳንድ የእስያ ሀገራትም የባህል ሀኪሞች ዘንድ ሌሎች መጠሪያ ስሞች አሉት::
ፈንገሱ የሚይዛቸው ንጥረነገሮችን ሙሉ በሙሉ ለይቶ ለማውጣት እስካሁን ለተመራማሪዎች አስቸጋሪ ቢሆንም ፈንገሱ እውነትም በኀል ህክምና ባለሞያዎቹ ይሰጣል የሚሏቸውን የጤና ጥቅሞች በከፊል ሊሰጥ እንደሚችል በጥናት ደርሰውበታል::
ይህ በአለም ዙሪያ በተለያየ መልክ ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ጋኖደርማ ሉሲደም የተሰኘ መሽሩም የሰውነት በሽታን የመከላከል አቅምን ማመጣጠን ፣ የደም ስኳር መጠንን ማስተካከልን ጨምሮ ፣ፀረ ካንሰር ፣ ፀረ ኢንፌክሽን ጥቅሞች ሲኖሩት ፣ የጉበት ጤንነትን የመጠበቅ ፣ የአልዛይመር በሽታ የተያዙ ሰዎችን መርዳት ወዘተ… ጥቅሞች ሊሰጥ እንደሚችል ሳይንቲስቶች በእንስሳት ላይ በሰሯቸው ጥናቶች አረጋግጠዋል::
ነገር ግን ይህ የባህል መድሀኒቶች ንጉስ ለመድሀኒትነት ቢውል በምን ያህል መጠን መወሰድ እንዳለበት እንዲሁም ለእንስሳት መሽሩሙን በመስጠት ሲሞከር የሚሰጣቸውን ጥቅሞች ለሰዎች መስጠቱን ለማረጋገጥ የበለጠ ጥናቶች ያስፈልጉታል:: በተጨማሪም ይሄ መሽሩም በነዚህና በሌሎች ምክንያቶች የተነሳ ከላይ የተጠቀሱትን በሽታዎች ለማከም እስካሁን በአለም የጤና ድርጅት ፈቃድ አልተሰጠውም::
በተጨማሪም በፖውደር መልክ የተዘጋጀ ሪሺ መሽሩም (ጋኖደርማ ሉሲደም) የከፋ የጉበት ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ጥናቶች ያመላክታሉ:: በተጨማሪም የአፍ የአፍንጫና የጉሮሮ መድረቅ ፣ ተቅማጥ ፣ማሳከክ ፣ሽፍታ፣ እራስ ምታት ፣ የአፍንጫ መድማት ወዘተን ሊያስከትል ይችላል::
Sources :-
https://www.ncbi.nlm.nih.gov/books/NBK92757/
https://www.researchgate.net/publication/337888378_Health_Benefits
Click Here to Find more Reviews on highly acclaimed Health Related Products
[email-subscribers-form id=”1″]