You are currently viewing በሁለት ሳምንታት ውስጥ 97,000 የአሜሪካ ህፃናት ኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል!

በሁለት ሳምንታት ውስጥ 97,000 የአሜሪካ ህፃናት ኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል!

በአሜሪካ በመጨረሻዎቹ የጁላይ ሁለት ሳምንታት ብቻ 97,000 ህፃናት ሳርስ-ኮቭ 2(ኮሮናቫይረስ) ተገኝቶባቸዋል::
በአሜሪካ እስካሁን ከተገኙት አምስት ሚልዮን ገደማ በሳርስ-ኮቭ 2 የተያዙ ሰዎች ከ338 ሺህ በላይ የሚሆኑት ህፃናት እንደሆኑ የአሜሪካን የሲቢኤስ ዜና አውታሩ ማይክል ጆርጅ ሪፖርት አድርጓል::

የተያያዘም በአሜሪካ ኮሮናቫይረስ በምርምራ የተገኘበት ሰው ከአምስት ሚልየን አልፏል።

ሬውተርስ ትናንት ቅዳሜ ምሽት ላይ አንደዘገበው በአሜሪካ ከ66 ሰው አንዱ ኮሮናቫይረስ አንደተገኘበት ገልፆ እስከአሁን በአጠቃላይ በሐገሪቷ ኮሮናቫይረስ የተገኘበት ሰው ቁጥር አምስት ሚልየን ሲያልፍ የሟቿች ቁጥር ከ160,000 በላይ ሆኗል።

የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጽ የሆኑት ፌስቡክና ትዊተር የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የተሳሳተ መረጃ አሰራጭተዋል በሚል በገፃቸው ላይ እርምጃ መውሰዳቸው ይታወሳል። እርምጃ የወሰዱትም ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የህፃናት የበሽታ መከላከል አቅም ከፍተኛ በመሆኑ ለኮሮናቫይረስ አይጋለጡም በሚል መረጃ በማሰራጨታቸው ነበር።

Leave a Reply