የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት የኮቪዴ-19 በሽታ ለመከላከልና በልዩ ትኩረት በሽታውን ለመቆጣጠር የሚያስችል ማህበረሰብ ንቅናቄ እና ምርመራ (ማንም) ዘመቻ፡ ‘ምክንያት አልሆንም’ በሚል መሪ ቃል ይፋ አድርገዋል፡፡
የ “ምክንያት አልሆንም!” ዋነኛ አላማ ማንኛውም ሰው ለኮሮናቫይረስ መስፋፋት ምክንያት ላለመሆን ራሱን የሚከላከልበት፣ ከራሱ አልፎ ቤተሰቡንና አካባቢውን የሚጠብቅበት እንዲሁም በተሰማራበት ሙያ ሁሉ ሃላፊነት በመውሰድ በእኔነት ስሜት ለራሱ ቃል የሚገባበት ነው፡፡